ኢንተርቪዥን ለአፍሪካውያን አርቲስቶች ዓለም አቀፍ ተደራሽነት በር ከፋች ነው - ድምፃዊት ፀደኒያ ገ/ማርቆስ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢንተርቪዥን ለአፍሪካውያን አርቲስቶች ዓለም አቀፍ ተደራሽነት በር ከፋች ነው - ድምፃዊት ፀደኒያ ገ/ማርቆስ
ኢንተርቪዥን ለአፍሪካውያን አርቲስቶች ዓለም አቀፍ ተደራሽነት በር ከፋች ነው - ድምፃዊት ፀደኒያ ገ/ማርቆስ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.09.2025
ሰብስክራይብ

ኢንተርቪዥን ለአፍሪካውያን አርቲስቶች ዓለም አቀፍ ተደራሽነት በር ከፋች ነው - ድምፃዊት ፀደኒያ ገ/ማርቆስ

ውድድሩ አፍሪካውያን ድምፃቸውን እና ታሪካቸውን በዓለም መድረክ፣ በአዲስ ታዳሚ፣ በአዲስ እድል እና በአዲስ ፈተና ፊት የሚያሳዩበት ነው ስትል ድምፃዊቷ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግራለች፡፡

በተወሰኑ አርቲስቶች የተገደበውን የዓለም አቀፍ መድረክ ተሳትፎ ለማስፋትና ተደራሽነተን ለማሳደግ እንደ ኢንተርቪዥን ያሉ ውድድሮች እድል ይሰጣሉ ብላለች፡፡

" የኢትዮጵያን ሙዚቃ ከፍተኛ አቅም ማሳየት እና ቀጣይ የስራ ህይወታቸውን ድንበር ተሻጋሪ አድርገው ትስስርን ለመገንባት ያስችላቸዋል፡፡ .... በተለይም ወጣቶች ከሀገር ውስጡ ባሻገር ማሰብ እንዲችሉ እድል ይሰጣቸዋል፡፡" በማለት የአፊሪማ እና ኮራ የሙዚቃ ሽልማቶች ባለቤቷ ደምፃዊት ፀደኒያ የኢንተርቪዥን ተሳትፎ አበርክቶን አስረድታለች፡፡

ኢንተርቪዝን ከሙዚቃ ውድድር ባሻገር የትስስር ድልድይን መገንቢያ፣ የዲፕሎማሲ መስክን ማስፊያ፣ ለትብብር በር ከፋችና አካታችነትን የሚያሳድግ መሆኑንም እውቋ ድምፃዊት ገልፃለች፡፡

"ሙዚቃ የዓለም ቋንቋ ነው። ስለ አሜሪካውያን፣ ስለ ብሪቲሽ ማለት ብቻ አይደለም፡፡ ባልተገደበና ሁሉንም አካታች ሆኖ ተደራሽ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ኢንተርቪዥን ከሩስያ ባሻገር ያሉ አርቲስቶችን ፣ ከእስያ የተሻገሩ ሀገራትን ያሳተፈ ነው፤ በዚሀም ነው እኔ የወደድኩት፡፡" ስትል ተናግራለች።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0