ዛምቢያ የ414 ሚሊዮን ዶላር የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን አጸደቀች
20:22 16.09.2025 (የተሻሻለ: 20:24 16.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ዛምቢያ የ414 ሚሊዮን ዶላር የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን አጸደቀች
የዛምቢያ የአካባቢጥበቃ አስተዳደር ኤጀንሲ 600 ሜጋ ዋት አቅም ያላቸውና በሦስት ወረዳዎች የሚገነቡ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን አጽድቋል።
ፕሮጀክቶቹ ይፋ የተደረጉት ኤጀንሲው ባካሄደው 35ኛው የአካባቢ ጥበቃ ምዘና ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ከ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር በላይ የሚያወጡ እና በተለያዩ ዘርፎች የሚተገበሩ ኢንቨስትመንቶችን በተመለከተበት ወቅት ነው።
“እነዚህ ፕሮጀክቶች በዛምቢያ የንፁህ ኢነርጂ ሽግግር ውስጥ ትልቅ ምዕራፍን ያመላክታሉ” ሲል የገለፀው ኤጀንሲው ፕሮጀክቶቹ በቅሪተ አካል ነዳጅ ላይ ያለውን ጥገኝነት በመቀነስ ሂደት ውስጥ ያላቸውን ሚና ጠቁሟል።
ማዕድን ማውጣት፣ ኢነርጂ፣ መሠረተ ልማት፣ ማኑፋክቸሪንግ እና ግብርናን ጨምሮ በአጠቃላይ 156 ፕሮጀክቶች ተገምግመዋል፡፡
ከእነዚህ ውስጥ የአካባቢ ጥበቃ መስፈርቶችን ባለማሟላታቸው ሁለት ፕሮፖዛሎች ውድቅ ተደርገዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X