“ኢትዮጵያ ለዘላለም የጂኦግራፊ እስረኛ ሆና ትኖራለች ብሎ የሚያስብ ኢትዮጵያዊ ካለ የሞተ ነው” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
19:06 16.09.2025 (የተሻሻለ: 19:24 16.09.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ“ኢትዮጵያ ለዘላለም የጂኦግራፊ እስረኛ ሆና ትኖራለች ብሎ የሚያስብ ኢትዮጵያዊ ካለ የሞተ ነው” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
“ኢትዮጵያ ለዘላለም የጂኦግራፊ እስረኛ ሆና ትኖራለች ብሎ የሚያስብ ኢትዮጵያዊ ካለ የሞተ ነው” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመደመር መንግሥት መጽሐፍ ምረቃ ንግግራቸው የባህር በርን አስመልክቶም የመውጫ በር ያስፈልገናል ሲሉ አጽናኦት ሰጥተዋል፡፡
“ኢትዮጵያ ለዘላለም የጂኦግራፊ እስረኛ ሆና ትኖራለች ብሎ የሚያስብ ኢትዮጵያዊ ካለ የሞተ ነው” ያሉ ሲሆን የመውጫ በር ያስፈልገናል፤ ይህንንም በሰላማዊ መንገድ ለማረጋገጥ በራችን ክፍት ነው ብለዋል።
በኑክሌር ሳይንስ የምናስመዘግበው ስኬት በግብርና እና በሌሎችም መስኮች ከምናካሂደው ልማት ወሳኝ ያሉ ሲሆን፣ ሩሲያ የዛሬ 80 ዓመት ያሳካችውን ዛሬ እውን እናደርገዋለን ስንል የሚጠራጠር ኢትዮጵያዊ አይኖርም ነው ያሉት።
የህዳሴው ግድብ በተመለከተም ኢትዮጵያ ለመላው ጥቁር ህዝብ ኩራት የሆነ ስኬት ያስመዘገበችበት መሆኑን ግለፀዋል፡፡ ግድቡ የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ስኬት መሆኑንም ጠቅሰዋል።
የዛሬ 10 ዓመት በእግር ኳስ በልጆቻችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የምንኮራበት ዘመን ይመጣል ያሉ ሲሆን ለዚህም መንግሥት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X