ግዙፉ የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ አፍሪካን ይበልጥ ወደ ዓለም ያቀርባል - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ሰብስክራይብ

ግዙፉ የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ አፍሪካን ይበልጥ ወደ ዓለም ያቀርባል - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

በዓመት 110 ሚሊየን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ያለው አዲሱ የቢሾፍቱ የአውሮፕላን ማረፊያ አኅጉሪቱን በማስተሳሰር ረገድ ጉልህ ሚና እንደሚጫወት የአየር መንገዱ የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊ ለማ ያደቻ ተናግረዋል።

ዋና ኃላፊው ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ የአውሮፕላን ማረፊው አገልግሎትን በሚያቀላጥፉ ስማርት ቴክኖሎጂዎች የሚደራጅ መሆኑን አንስተዋል።

"አዲሱ ኤርፖርት በሰው ሠራሽ አስተውሎት እና ሮቦቲክስ የዳበረ ስማርት ኤርፖርት ነው።ይህም አኅጉሪቱ ከዓለም ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ግንኙነት ያቀላጥፋል" ብለዋል።

ኃላፊው ስለ አዲሱ አየር ማረፊያ ከተናገሩት ተጨማሪ ነጥቦች

በዓመት 3.73 ሚሊየን ቶን ጭነት የማስተናገድ አቅም አለው፡፡

ከስምጥ ሸለቆዋ ቢሾፍቱ ስነ-ምህዳር ጋር የተስማማ አረንጎዴ ገጽታ ይላበሳል፡፡

ከአዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ጋር በፈጣን ባቡር ይተሳሰራል።

ኢትዮጵያ ከብሪክስ አባል አገራት ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ግንኙነት የማሳደግ አበርክቶው የጎላ ነው፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0