የ22 ሰብሎች 90 ዝርያዎችን እያባዛ መሆኑን የኢትዮጵያ ግብርና ስርዎች ኮርፖሬሽን አስታወቀ
16:33 16.09.2025  (የተሻሻለ: 16:34 16.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
 / ሰብስክራይብ
የ22 ሰብሎች 90 ዝርያዎችን እያባዛ መሆኑን የኢትዮጵያ ግብርና ስርዎች ኮርፖሬሽን አስታወቀ
ኮርፖሬሽኑ ባሉት ስድስት የምርጥ ዘር ማባዣ አርሻ ልማት ጣቢያዎች፣ በክላስተር በተደራጁ አርሶ አደሮች ማሳ፣ በመንግሥትና በግል እርሻዎች የዘር ማብዛት ስራዎች እያከናወነ መሆኑን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሚቀርበው የምርጥ ዘር ፍላጎት 33 በመቶ ማሟላቱን የገለፀው ኮርፖሬሽኑ በዓመት በአማካይ ከ450 ሺህ ኩንታል በላይ ዘር ለተጠቃሚዎች እየቀረበ ነው ብሏል፡፡
በ2016/17 የምርት ዘመን 20 ሺህ 627 ሄክታር መሬትን በዘር በመሸፈን ከ460 ሺህ በላይ ምርት ማግኘት መቻሉም ተገልጿል፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X