የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አዲሱ ‘የመደመር መንግሥት’ መጽሐፍ እየተመረቀ ነው

ሰብስክራይብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አዲሱ ‘የመደመር መንግሥት’ መጽሐፍ እየተመረቀ ነው

‘የመደመር መንግሥት’ መጽሐፍ በ3 ዋና ዋና ክፍሎች በ418 ገፆች እና በ13 ምዕራፎች የተዋቀረ ነው።

የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍጹም አሰፋ ባቀረቡት የመጽሐፍ ዳሰሳ በጠቅላይ ሚንስትሩ በተጻፉት አራት መጻሕፍት መካከል ስላለው ትስስር ምልከታቸውን አካፍለዋል።

ዶ/ር ፍጹም በዳሰሳቸው “ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በመጽሐፋቸው እንደ አገር እንዴት ኋላ ቀረን የሚለውን ጉዳይ ፈትሸው ህዝባችንን እንዴት ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና እናድርሰው የሚለውን መፍትሄ አስቀምጠዋል።” ብለዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ጌታቸው ረዳ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ እና ሌላው የፍልስፍና ምሁር ዘሪሁን ተሾመ በመጽሐፉ ዙሪያ ያላቸውን ምልከታ ለታዳምያን አካፍለዋል።

ምሁራኑ ከተለያዩ ዘመናት ዓለም አቀፋዊ ፖለቲካዊ እሳቤዎች እና ፍልስፍናዎች፣ ዓለም አቀፋዊ ገቢራዊ ሁኔታዎች እና በኢትዮጵያ እየተመዘገቡ ካሉ ተጨባጭ ለውጦች አንጻር የመጽሐፉን ይዘት ተንትነዋል።

በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች እና የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተወካዮች ተገኝተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አዲሱ ‘የመደመር መንግሥት’ መጽሐፍ እየተመረቀ ነው - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አዲሱ ‘የመደመር መንግሥት’ መጽሐፍ እየተመረቀ ነው - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0