ኢንተርቪዥን 'ፂም ያላቸው ወንዶች በሴቶች ቀሚስ' ከሚታዩበት ዩሮቪዥን የሚሻገር ምርጫን ያቀርባል - ላቭሮቭ

ሰብስክራይብ

ኢንተርቪዥን 'ፂም ያላቸው ወንዶች በሴቶች ቀሚስ' ከሚታዩበት ዩሮቪዥን የሚሻገር ምርጫን ያቀርባል - ላቭሮቭ

"ዩሮቪዥንን ከወደዳችሁ፤ ተመልከቱት። ነገር ግን አሁን ባህልን፣ ወግ እና የሞራል እሴቶችን የመጠበቅ ከፍተኛ ፍላጎት አለ፡፤ ይህም የሚያበረታታ ነው።" ሲሉ የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ መስከረም 10 የሚካሄደውን የኢንተርቪዥን 2025 ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ውድድር አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት ተናግረዋል።

የሰርጌ ላቭሮቭ ቁልፍ መግለጫዎች፡-

ሞስኮ ውስጥ "ወዳጅ ያልሆኑ ሀገሮች" የሚለው ቃል አጠቃቀም ቀስ በቀስ እየተለወጠ ነው። አሁንም ጥቅም ላይ ሲውል ስሜቱ "ከሩሲያ ጋር የማይስማሙ መንግስታት" ብቻ ማለት ነው እንጂ የማይስማሙ ሀገሮች የሉም።"

አንዳንድ ሀገራት ለባህል እና ለኪነጥበብ ሳይገደቡ መንግስታቸውን ቢመሰርቱ የራሳቸው ጉዳይ ነው የሚሆነው፣ ይህን ደግሞ ሩሲያ ከምትከተለው ልምድ ጋር በማነፃፀር የባህል እድገትን ለማበረታታት እንደ "የተከበሩ" ወይም "የህዝብ አርቲስት" ማዕረግ የመስጠት ልምድ፣ እንደ አሜሪካ ወይም እንግሊዝ ባሉ ሀገራት የሚታይ አይደለም።

ሩሲያ ከአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) ከመፍረሱ በፊት ካደረጋቸው ግባራት በተቃራኒ በሌሎች መንግስታት ላይ ተጽእኖ የማድረግ ዓላማ የላትም።

የሩሲያ አካሄድ ስፖርትን፣ ኪነ ጥበብን ወይም ማንኛውንም የሰው ልጅ እንቅስቃሴን የፖለቲካ ግቦችን ማሳኪያ አድርጎ ለመጠቀም ከሚደረገው ሙከራ ፍጹም የተለየ ነው።

በእንግሊዝኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0