ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የስፖርት ትብብራቸውን ለማሳደግ ተስማሙ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ እና ሩሲያ የስፖርት ትብብራቸውን ለማሳደግ ተስማሙ
ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የስፖርት ትብብራቸውን ለማሳደግ ተስማሙ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.09.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የስፖርት ትብብራቸውን ለማሳደግ ተስማሙ

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቀጣይ ወራት በሚካሄዱ የሳማራ እና ሞስኮ ማራቶኖች ላይ እንዲሳተፉ ሩስያ ጥሪ አቅርባለች፡፡

የሩስያ ስፖርት ሚኒስትር ድያግተረቭ ቭላድሚሮቪች ከኢትዮጵያ ባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልማህዲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ጥሪውን ያቀረቡ ሲሆን ሁለቱ ሀገራት በዘርፉ በትብብር ሊሰሩባቸው በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ተነጋግረዋል፡፡

ሚኒስተር ዴኤታዋ በበኩላቸው በአትሌቲክስ ብሎም በእግር ኳሱ የወዳጅነት ጨዋታዎችን በማዘጋጀት በዘርፉ በትብብር ሊሰሩባቸው የሚችሉባቸውን ዘርፎች ጠቁመዋል፡፡

ድያግተረቭ አክለውም በስፖርት ዘርፍ ማጥናት የሚፈልጉ ተማሪዎችን በ14 የሩስያ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ማስተማርና የመቀበል ምጣኔውን ለማሳደግ ዝግጁነታቸውን ገልፀዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የስፖርት ትብብራቸውን ለማሳደግ ተስማሙ - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የስፖርት ትብብራቸውን ለማሳደግ ተስማሙ - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0