ስፑትኒክ አፍሪካ በጥቂት ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ስር ለወደቀው የትርክት ቀረፃ የዓተያይ ብዝኃነት የፈነጠቀ ነው - አምባሳደር ነብዩ ተድላ

ሰብስክራይብ

ስፑትኒክ አፍሪካ በጥቂት ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ስር ለወደቀው የትርክት ቀረፃ የዓተያይ ብዝኃነት የፈነጠቀ ነው - አምባሳደር ነብዩ ተድላ

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተሩ ሚዲያው ቢሮውን በአዲስ አበባ መክፈቱ፣ የአፍሪካን ታሪክ እና እውነት ከምንጩ በመተረክ አማራጭ አመለካከቶች ቦታ እንዲያገኙ እንደሚያስችልም ገልጸዋል፡፡

" የስፑትኒክ አፍሪካ በአዲስ አበባ መገኘት ከሚዲያ ስርጭት የተሻገረ ዘርፈ ብዙ ትርጉም አለው። ሚዲያው በሰብአዊነት፣ በባሕሎች እና በሥልጣኔዎች መካከል ድልድይ ሆኖ እንደሚያገለግልም አምናለሁ" ብለዋል።

አምባሳደር ነብዩ ከስፑትኒክ አፍሪካ በነበራቸው ቆይታ ሚዲያው አፍሪካዊያን ሩሲያን ይበልጥ እንዲያውቁ ያለውን እገዛም አንስተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0