እስራኤል ጋዛ ከተማን ለመያዝ ጥቃት ጀምራለች፤ እስካሁን የታወቁ መረጃዎች

ሰብስክራይብ

እስራኤል ጋዛ ከተማን ለመያዝ ጥቃት ጀምራለች፤ እስካሁን የታወቁ መረጃዎች

ሰኞ ዕለት የእስራኤል ጦር ጋዛ ከተማን ለመያዝ የመሬት ጥቃት ጅምሯል (አክሲዮስ በሥም ያልተጠቀሱ የእስራኤል ባለሥልጣናትን ለዘገባው ዋቢ አድርጓል)።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ኢየሩሳሌም ተገኝተው የእስራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ካገኙ እና ዘመቻውን ከደገፉ በኋላ ጥቃቱ ተከፍቷል (አክሲዮስ)።

የዘመቻው መጀመር ተረጋግጧል (የእስራኤል እና የፍልስጤም ሚዲያዎች ዘግበውታል)።

የእስራኤል ታንኮች መግባታቸውን ተከትሎ ሰኞ ምሽት በከተማዋ እና በዙሪያዋ ከፍተኛ የአየር ጥቃት እና የመድፍ ተኩስ እንደነበረ ከጋዛ የወጡ ዘገባዎች ጠቁመዋል (ዘ ጀሩሳሌም ፖስት)።

የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት፣ ባለፉት ጥቂት ቀናት በከተማዋ እና በአካባቢዋ የአየር ጥቃቶችን ቀስ በቀስ እያሰፋ ሲሆን፣ አርብ ዕለት ሃማስ ለወታደራዊ አገልግሎት ይጠቀማቸዋል ያላቸውን በጋዛ ከተማ የሚገኙ ረዣዥም ሕንጻዎች አፍርሷል (ዘ ጀሩሳሌም ፖስት)።

ጋዛ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ሁሉም ሰዎች ከተማዋን እንዲለቅቁ ሲጠይቅ የነበረው የእስራኤል ጦር፣ በቅርብ ሳምንታት ውስጥ 300 ሺህ የሚሆኑ ፍልስጤማውያን ከከተማዋ ቢሸሹም 700 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች እንደቀሩ ገልጿል።

“ጋዛ እየተቃጠለች ነው… ተልዕኮው እስኪጠናቀቅ ድረስ አንቆምም፣ ወደኋላም አንመለስም” ሲሉ የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር፣ እስራኤል ካትዝ ማክሰኞ ማለዳ ላይ በኤክስ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ፣ ታጋቾችን፣ ወታደሮችን እና ሲቪሎችን ጉዳት ለመቀነስ ተስፋ አድርገው የቆዩትን የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ዋና አዛዥ አያል ዛሚርን ጨምሮ ከዋና ዋና የጸጥታ ኃላፊዎች ተቃውሞ ቢያጋጥማቸውም በወረራው ገፍተውበታል(ዘ ጀሩሳሌም ፖስት)።

እስካሁን የተሰጡ ምላሾች

የአስራኤል ሚዲያዎች እንደዘገቡት በጋዛ ታግተው የሚገኙ ታጋቾች ቤተሰቦች ከኔተንያሁ ይፋዊ መኖሪያ ቤት ውጭ ተቃውሞ ጀምረዋል፡፡

የታጋቾች እና የጠፉ ቤተሰቦች ፎረም በጋዛ ውስጥ ውጊያውን የማባባስ እርምጃውን በጽኑ አውግዟል፤ "ከ710 የምርኮ ሌሊቶች በኋላ፣ ይህ የታጋቾች ማብቂያ ሊሆን ይችላል። ኔተንያሁ ለሰዎቹ እጣ ፈንታ እና የሞቱትን በክብር ለመመለስ የግል ኃላፊነት አለባቸው" በማለትም አስጠንቅቋል፡፡

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ሃማስ ታጋቾችን ይዞ እያዘዋወረ ያለው "በእስራኤል የመሬት ጥቃት በሰው ጋሻነት (ጥይት ማብረጃነት) ለመጠቀም ነው" ሲሉ ማኅበራዊ ሚዲያቸው ላይ ከስሰዋል።

ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኙ ምስሎች

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
እስራኤል ጋዛ ከተማን ለመያዝ ጥቃት ጀምራለች፤ እስካሁን የታወቁ መረጃዎች - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
እስራኤል ጋዛ ከተማን ለመያዝ ጥቃት ጀምራለች፤ እስካሁን የታወቁ መረጃዎች - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0