የኢየሩሳሌም ፓትርያርክ ከኢትዮጵያው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ናትናኤል ጋር ተወያዩ
19:52 15.09.2025 (የተሻሻለ: 19:54 15.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢየሩሳሌም ፓትርያርክ ከኢትዮጵያው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ናትናኤል ጋር ተወያዩ
ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ በኢየሩሳሌም ለምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን አዲስ የተሾሙትን አቡነ ናትናኤልን ተቀብለው አነጋግረዋል።
አቡነ ናትናኤል ለፓትርያርኩ ያላቸውን አክብሮት እና ከመንበረ ፓትርያርኩ ጋር ለመተባበር ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ፓትርያርኩም በዴር ሡልጣን አብርሃም ገዳም ምክንያት የኢትዮጵያ እና የግብጽ ቤተክርስቲያን መካከል ያለውን ችግር ለመፍታት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማድረግ እና ከኢትዮጵያ ቤተ-ክርስቲያን ጋር ለመተባበር ያላቸውን ፍላጎት አሳውቀዋል።
ፓትሪያርኩ ከሰርቢያ የመጡ 30 የሃይማኖት ተጓዦች ቡድንን፣ በኢየሩሳሌም የሚገኙት የግሪክ ቆንስላ ጄኔራል ዲሚትሪዮስ አንጀሎፑሎስን፣ ከሞንቴኔግሮ የመጡ የአይሁድ ተወካዮች ቡድን እንዲሁም የቤልጂየም አዲስ ቆንስላ ጄኔራል አኒክ ቫን ካልስተር ተቀብለው አነጋግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/2
© telegram sputnik_ethiopia

2/2
© telegram sputnik_ethiopia
1/2
© telegram sputnik_ethiopia
2/2
© telegram sputnik_ethiopia