ለ2018 የትምህርት ዘመን የተመዘገቡ ተማሪዎች ቁጥር ወደ 22 ሚሊዮን ከፍ ማለቱን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ
17:11 15.09.2025 (የተሻሻለ: 17:14 15.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ለ2018 የትምህርት ዘመን የተመዘገቡ ተማሪዎች ቁጥር ወደ 22 ሚሊዮን ከፍ ማለቱን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እሰከ ትናንትናው ዕለት ድረስ የተመዘገቡት ተማሪዎች ቁጥር 22 ሚሊዮን 479 ሺህ 299 የደረሰ ሲሆን ይህም ቁጥር ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተመዘገቡት 15.3 ሚሊዮን ተማሪዎች ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል ብለዋል።
ሚኒስትሩ ለውጡ የመጣው ከዚህ ቀደም ግጭትን ጨምሮ በተለያዩ ምክንያቶች በተፈጠረው መስተጓጎል ምክንያት ትምህርታቸውን አቋርጠው የነበሩ ሕጻናት ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመለሱ በጋራ የተደረገው ጥረት ውጤት እንደሆነ አመላክተዋል።
ምዝገባው አሁንም እንደቀጠለ በመሆኑ፤ የመጨረሻው የተማሪዎች ቁጥር በቀጣይ ቀናት የበለጠ ከፍ ሊል እንደሚችል ማስረዳታቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X