በሞስኮ የኢትዮጵያ ባሕሎች የደመቁበት የፊልሃርመኒክ አዳራሽ ድግስ

ሰብስክራይብ

በሞስኮ የኢትዮጵያ ባሕሎች የደመቁበት የፊልሃርመኒክ አዳራሽ ድግስ

በኢትዮጵያ የባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር አዘጋጅነትና በሻኩራ ፕሮዳክሽን አስተባባሪነት ወደ ሞስኮ ያቀናው ኪን-ኢትዮጵያ ቡድን በሩስያ ሁለተኛ መድረኩን በልዩ ድምቀት ተካሂዷል።

በመድረኩ የኢትዮጵያን ቱባ ባሕል የሚያሳዩ ባሕላዊ ሙዚቃ፣ ውዝዋዜ፣ የባሕል አልባሳት ትዕይንተ-ፋሽን እንዲሁም የሰርከስ ትርዒት ቀርቧል።

ዝግጅቱን ሩሲያውያን፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት፣ ኢትዮጵያውያን እና በሩሲያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ታድመውታል፡፡

የመድረክ ሥራዎቹ ከመቅረባቸው አስቀድሞ ተሳታፊዎች የኢትዮጵያን ቡና እንዲያጣጥሙ ተድርጓል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0