የአማጺ መሪው ኮኒ ፍርድ ለ20 ዓመታት መዘግየት ስለ ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ‘ውጤታማነት’ በብዙ ይናገራል - ናይጄሪያዊ የሕግ ባለሙያው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአማጺ መሪው ኮኒ ፍርድ ለ20 ዓመታት መዘግየት ስለ ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ‘ውጤታማነት’ በብዙ ይናገራል - ናይጄሪያዊ የሕግ ባለሙያው
የአማጺ መሪው ኮኒ ፍርድ ለ20 ዓመታት መዘግየት ስለ ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ‘ውጤታማነት’ በብዙ ይናገራል - ናይጄሪያዊ የሕግ ባለሙያው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.09.2025
ሰብስክራይብ

የአማጺ መሪው ኮኒ ፍርድ ለ20 ዓመታት መዘግየት ስለ ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ‘ውጤታማነት’ በብዙ ይናገራል - ናይጄሪያዊ የሕግ ባለሙያው

የዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ወጥነት በሌለው ትኩረቱና ውጤታማ ባልሆኑ አሰራሮቹ ምክንያት ቅቡልነቱን አጥቷል ሲሉ የዛሬፋት ኤይድ ግብረሰናይ ድርጅት መሥራች ቤን አብርሃም ተናገሩ

"ፍትሕ ፍትሐዊ እንደሆነ መታየት አለበት። ማንም ብትሆን፣ ምንም ብትሆን እንዲሁም እንዴትም ብትሆን ከሕግ በላይ አይደለህም” ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

አብርሃም አስተያየቱን የሰጡት የዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት በኡጋንዳው የአማፂ መሪ ጆሴፍ ኮኒ ላይ የእስር ማዘዣ ከወጣ ከ20 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ችሎት ሊጀምር መሆኑን ተከትሎ ነው። ኮኒ አሁንም ድረስ በቁጥጥር ስር አልዋለም።

የሕግ ባለሙያው መዘግየቱን “ለእውነተኛ ማሻሻያ መሠረት” ሲሉ ገልፀው፣ ፍርድ ቤቱ ለተጎጂዎች በወቅቱ ፍትሕ መስጠት አለመቻሉን አጽንዖት ሰጥተዋል።

አብርሃም “የአፍሪካ ሕብረት አባላት በፍርድ ቤቱ ኢ-ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ኢላማ እንደተደረጉ ስለሚሰማቸው ከዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ለመውጣት ድጋፋቸውን እየገለፁ ነው” ብለዋል። “አፍሪካ ብቻ ጦርነት የሚካሄድባት ቦታ የሆነች ይመስል በአፍሪካ፣ በጦርነቶቿ እና በወንጀሎቿ ላይ ያልተመጣጠነ ትኩረት ሲደረግ እናያለን።”

ማሊ፣ ኒጀር እና ቡርኪና ፋሶ አማራጭ የሆነ ቀጣናዊ ፍርድ ቤት ለማቋቋም የሚያደርጉትን ጥረት ደግፈዋል። አብርሃም ይህን ተነሳሽነት “አድናቆት የሚቸረው” እና ራሱን የቻለ የፍትሕ አሠራር ሞዴል ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል።

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0