ሩሲያ ከቡድን 20 ሀገራት መሃከል ዝቅተኛውን የሥራ አጥነት መጠን አስመዘገበች
14:13 15.09.2025 (የተሻሻለ: 14:14 15.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ ከቡድን 20 ሀገራት መሃከል ዝቅተኛውን የሥራ አጥነት መጠን አስመዘገበች
ስፑትኒክ በብሔራዊ ስታትስቲክስ መረጃ ላይ በሠራው ትንተና መሠረት፤ በሁለተኛው ሩብ ዓመት መጨረሻ ላይ የነበረው የሩሲያ የሥራ አጥነት መጠን 2 ነጥብ 2 በመቶ ብቻ የነበረ ሲሆን፣ ይህም ከመጋቢት ወር (የመጀመሪያው ሩብ ዓመት) ጋር ሲነጻጸር መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል።
በሌሎች የቡድን 20 አባል ሀገራት ውስጥ ያለው የሥራ አጥ ቁጥር አካሄድ፦
በሜክሲኮ ያለው የሥራ አጥነት መጠን ወደ 2.7 በመቶ ከፍ ብሏል።
በጃፓን የሥራ አጥነት መጠን በ2.5 በመቶ ጸንቶ ቆይቷል።
በደቡብ ኮሪያ ያለው የሥራ አጥነት መጠን ወደ 2.6 በመቶ መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል።
ደቡብ አፍሪካ ብቸኛዋ ባለሁለት አኃዝ የሥራ አጥነት መጠን 33.2 በመቶ ያላት ሀገር ሆናለች።
በቱርክ የሥራ አጥነት መጠን ወደ 8.4 በመቶ ከፍ ብሏል።
በተቃራኒው ሕንድ -2.3 በመቶ እና ብራዚል -1.2 በመቶ የሥራ አጥነት መጠን ላይ የሚታይ ቅናሽ አሳይተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X