በአልጄሪያ የካቢኔ ሹም ሽር አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የኃይል ሚኒስትር ተሹመዋል
13:45 15.09.2025 (የተሻሻለ: 13:54 15.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በአልጄሪያ የካቢኔ ሹም ሽር አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የኃይል ሚኒስትር ተሹመዋል
ፕሬዝዳንት አብደልመጂድ ተቡኔ በሰጡት መግለጫ፤ ሲፊ ግሪብን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሁም ሙራድ አጅልን የኢነርጂ እና ታዳሽ ኃይል ሚኒስትር አድርገው ሾመዋል።
ባለፈው ወር የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ናዲር ለርባዊን ከሥልጣን ከለቀቁ በኋላ ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት እና ከዚህ በፊት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር የነበሩት ግሪብ አሁን በቋሚነት የጠቅላይ ሚኒስትርነትን ሥልጣን ተረክበዋል። አጅል በበኩላቸው ከዚህ ቀደም የአልጄሪያ የመንግሥት የኃይል ኩባንያ የሆነው ሶኔልጋዝ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ ወደ ካቢኔው ተቀላቅለዋል።
የፕሬዝዳንቱ ጽሕፈት ቤት እንዳረጋገጠው የገንዘብ፣ የንግድ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በነበሩት ሥልጣን ላይ ይቀጥላሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X