በግብጽ የሚገኘው የሩሲያ የኢንዱስትሪ ዞን ወደ አፍሪካ ምቹ መግቢያ ይሆናል - የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
12:55 15.09.2025 (የተሻሻለ: 13:04 15.09.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበግብጽ የሚገኘው የሩሲያ የኢንዱስትሪ ዞን ወደ አፍሪካ ምቹ መግቢያ ይሆናል - የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በግብጽ የሚገኘው የሩሲያ የኢንዱስትሪ ዞን ወደ አፍሪካ ምቹ መግቢያ ይሆናል - የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
“በርካታ ሀገራት በግብጽ የስዊዝ ካናል ኢኮኖሚክ ዞን ውስጥ ገብተዋል፤ አካባቢያቸውንም እያለሙ ነው። አካባቢው ከኤይን ሶክና የባሕር ወደብ፣ ከባቡር መስመሮች እና መንገዶች አንጻር ምቹ ቦታ ላይ ይገኛል” ሲሉ አሌክሲ ኦቨርቹክ ተናግረዋል።
በትናትናው ዕለት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ የሩሲያ ልዑካን ቡድን ካይሮ ገብቷል። በልዑካን ቡድኑ ውስጥ በግብጽ በሚገኘው የሩሲያ የኢንዱስትሪ ዞን ውስጥ ለመሥራት ፍላጎት ያላቸው የሩሲያ ሥራ ፈጣሪዎችና የንግድ ማኅበራት ተወካዮች ተካትተዋል።
ወደ ግብጽ የኢኮኖሚ ዞን የተደረገው ጉብኝት ጥቅሞቹን በጋራ ለመገምገም ያስችላል ሲሉ ኦቨርቹክ ተናግረዋል።
ግብጻውያን ለኢኮኖሚ ዞኑ ነዋሪዎች የሚሰጡት ጥቅሞች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
🟠 የሥራ ሁኔታዎች፣
🟠 የመሠረተ ልማት ዝግጁነት እና
🟠 የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎች።
ኦቨርቹክ በዞኑ ላይ የሚደረግ ቀጥተኛ ግምገማ የንግድ ተቋማት አቅማቸውን እንዲፈትሹ እና ዞኑን በኢንቨስትመንት ዕቅዶቻቸው ውስጥ ለማካተት ወሳኝ እንደሚሆን አጽንኦት ሰጥተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X