'ወንጀለኛውን የእስራኤል የጦርነት ማሽን አስቁሙ ' ሲሉ የአረብ ሊግ ዋና ፀሐፊ ተናገሩ

ሰብስክራይብ

'ወንጀለኛውን የእስራኤል የጦርነት ማሽን አስቁሙ ' ሲሉ የአረብ ሊግ ዋና ፀሐፊ ተናገሩ

አሕመድ አቡል ጌት በዶሃ በተካሄደው የአረብ እና የሙስሊም ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ቀጥተኛ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አቅርበዋል።

"ወንጀለኛውን የእስራኤል ወታደራዊ ማሽን ከዚህ አሳፋሪ ጦርነት ማስቆም ላይ ሁላችንም ትኩረት ማድረግ አለብን” ብለዋል።

እስራኤል በኳታር ለፈፀመችው የአየር ጥቃት “ቆራጥ እርምጃ” መውሰድ እንደሚያስፈልግ እና ከኳታር መንግሥት ጋር “የአረብ-እስላማዊ ትብብርን” ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

ይህ መግለጫ እስራኤል አሜሪካ ባቀረበችው የሰላም ሐሳብ ላይ ለመወያየት በዶሃ ተሰብስበው በነበሩ የሃማስ መሪዎች ላይዘመቻ "የአሳት ጉባኤ" በሚል ጥቃት ከሰነዘረች በኋላ የመጣ ነው። እስራኤል ለጥቃቱ ኃላፊነት ብትወስድም የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ በበኩላቸው “ያልታሰበ አደጋ” ሲሉ ገልፀውታል።

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0