የሩሲያ ባሕር ኃይል ላይ ዚርኮን ሃይፐርሶኒክ ሚሳኤልን በባሬንትስ ባሕር በተደረገ ኢላማ ላይ ሞከረ
10:53 15.09.2025 (የተሻሻለ: 10:54 15.09.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ ባሕር ኃይል ላይ ዚርኮን ሃይፐርሶኒክ ሚሳኤልን በባሬንትስ ባሕር በተደረገ ኢላማ ላይ ሞከረ
በዛፓድ-2025 ስትራቴጂካዊ ልምምዶች ላይ፣ የጦር መርከብ አድሚራል ጎሎቭኮ በባሬንትስ ባሕር ውስጥ በተዘጋጀ የጠላት የባሕር ኃይል ኢላማ ላይ የዚርኮን ሃይፐርሶኒክ ሚሳኤልን በተሳካ ሁኔታ ማስወንጨፉን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቋል፡፡
ኢላማው በቀጥታ በመመታት መውደሙን በተደረገው ክትትል ተረጋግጧል። ጥቃቱ የ’ኖርዘርን ፍሊት’ (የሰሜናዊው መርከብ) የተለያዩ ኃይሎችን በማሳተፍ በአምሳለ ጠላት ላይ የተደረገ ሰፊ ዘመቻ አካል ነበር።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር እንደገለፀው፣ ልምምዶቹ የባሕር ዳርቻ ተቋማት እና በወታደራዊ ካምፖች መከላከል፣ እንዲሁም ትክክለኛ፣ የላቁ እና ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎችን ሥርዓትን የተቀናጀ አጠቃቀምን ጨምሮ የስብጥር ኃይሎችን ማሰባሰብ ዕዝ ልምምድንም አካትተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X