200 የሚጠጉ ለአደጋ የተጋለጡ የግብጽ ኤሊዎች ታይላንድ ውስጥ መያዛቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ
20:35 14.09.2025 (የተሻሻለ: 20:44 14.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
200 የሚጠጉ ለአደጋ የተጋለጡ የግብጽ ኤሊዎች ታይላንድ ውስጥ መያዛቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ
ባለፈው ሳምንት የ40 ዓመቱ ግብጻዊ ግለሰብ፣ ታይላንድ ሱቫርናብሁሚ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ለአደጋ የተጋለጡ በሕይወት ያሉ ኤሊዎችን በሻንጣው ደብቆ ወደ ላኦስ በሕገ-ወጥ መንገድ ሊያዘዋውር ሲሞክር በቁጥጥር ስር ውሏል።
ሰውዬው ሻንጣው ሲፈተሽ 187 የሚሆኑ በሕይወት ያሉ ኤሊዎች እና ሁለት የሞቱ ኤሊዎች ተገኝተዋል። ለእንስሳቱ ምንም ዓይነት ሕጋዊ የኤክስፖርት ሰነድ ማቅረብ አልቻለም።
ሕገ-ወጥ አዘዋዋሪው ለተጨማሪ ምርመራ እና ክስ ለኤርፖርት ፖሊስ ተላልፏል። የተያዙት ኤሊዎች ለዱር እንስሳት ጥበቃ ቢሮ ተሰጥተው ከተላለፉ በኋላ ወደ መኖሪያቸው ይመለሳሉ ተብሏል።
ምስል፡ የታይላንድ ብሔራዊ ፓርኮች፣ የዱር እንሰሳት እና የእፅዋት ጥበቃ መምሪያ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X