ከኢምግሬሽን ባሻገር፤ የቀድሞ ዲፕሎማት የለንደን ተቃውሞዎች መሠረታዊ መንስኤዎችን ገልፀዋል
19:21 14.09.2025 (የተሻሻለ: 19:34 14.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ከኢምግሬሽን ባሻገር፤ የቀድሞ ዲፕሎማት የለንደን ተቃውሞዎች መሠረታዊ መንስኤዎችን ገልፀዋል
የቀድሞ በሶሪያ የብሪታንያ አምባሳደር ፒተር ፎርድ፣ በሳምንቱ መጨረሻ በለንደን የተደረጉ ተቃውሞዎች ስለ ኢምግሬሽን ብቻ እንዳልነበሩ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
እነዚህ ተቃውሞዎች ከብሪኤግዚት እስከ የኑሮ ውድነት አንስቶ እስከ ብልሹ የኅብረተሰብ አገልግሎቶች ድረስ፣ “ስኬታማው መንግሥት አገሪቱን እየመራ ስላለበት አጠቃላይ አቅጣጫ እውነተኛ እና ምክንያታዊ ስጋትን” እንደሚያንፀባርቁ ገልጸዋል።
በተመሳሳይ ፎርድ “እንደ ጦስ-ዶሮ ስደተኞች ላይ የተደረገው ጤናማ ያልሆነ ትኩረት፣ በአጋጣሚ ተጠቃሚ ሰርጎ ገቦች የተቀጣጠለ ነው” ሲሉ አስምረውበታ።
የብሪታንያ መንግሥታት “ለሕዝብ ፍላጎት ጆሮአቸው እንደማይሰማ” እና የሌበር ፓርቲ መንግሥት ደግሞ “ተቃውሞን ለማዳፈን ሲለ የንግግር ነጻነትን ለማፈን” እንደተጠቀመበት ከስሰዋል።
ተቃዋሚዎች የእንግሊዝ እና የ”ዩኒየን” ሰንደቅ ዓላማዎችን ይዘው በጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር ላይ ድምጽ ማሰማታቸውን የጠቀሱት ፎርድ፣ ምላሽ ለመስጠት ለካቢኔው ጥቂት አማራጮች እንዳሉት አሳስበዋል፡፡ “የብሪታንያ መንግሥታት ግዙፍ የሕዝብ ተቃውሞዎችን ችላ ማለትን የለመዱ ናቸው” ሲሉ አክለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X