በናይጄሪያ የተዘጋጀው የአልቤኒዝም የቁንጅና ውድድር አሸናፊ ልዩ ንግሥት ዘውድ ደፋች

ሰብስክራይብ

በናይጄሪያ የተዘጋጀው የአልቤኒዝም የቁንጅና ውድድር አሸናፊ ልዩ ንግሥት ዘውድ ደፋች

ለመጀመሪያ ጊዜ ሌጎስ ውስጥ በተካሄደው ልዩ ውድድር በአልቤኒዚም (በተፈጥሮ ቆዳ፣ ዓይን እና ጸጉርን ነጭ የሚያድርግ ክስተት) ዙሪያ ያለውን ግንዛቤ ለማሳደግ ያስችላል ተብሏል።

አዲሷ ንግሥት አኒታ ቺዳይቡቤ ዳይኬ አልቢኒዝም አስመልክቶ ሕብረተሰቡ ያለውን ግንዛቤ የማሳደግ እቅድ ይዛለች።

“መጀመሪያ ቅድሚያ የምሰጠው ነገር፣ አልቢኒዝም ያለባቸው ሰዎች በማሕበረሰባችን ውስጥ ያላቸውን ጥንካሬ እና አዎንታዊ ተጽእኖ የሚያሳይ ማራኪ ይዘት መፍጠር ነው” ብላለች።

በናይጄሪያ ወደ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ከአልቢኒዝም ጋር የሚኖሩ ሲሆን፤ በተለምዶአዊ አፈ-ታሪኮች እና ጭፍን ጥላቻ ምክንያት ከአገልግሎት መገለል እና የጥቃት ድርጊቶች ይደርስባቸዋል። መንግሥት መድልዎን ለመዋጋት እና የሕብረተሰቡን ተቀባይነት ለማሳደግ ቃል ገብቷል።

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0