ናይጄሪያ የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራምን ከትምህርት ውጭ ላሉ ሕጻናት ለማስፋት አቅዳለች
17:26 14.09.2025 (የተሻሻለ: 17:34 14.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ናይጄሪያ የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራምን ከትምህርት ውጭ ላሉ ሕጻናት ለማስፋት አቅዳለች
በ2026 50 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለማድረስም የተወጠነው ማስፋፊያ በግንቦት ወር በተጀመረው እና በመጀመሪያ 20 ሚሊዮን ከትምህርት ቤት ውጭ ያሉ እና በቂ አገልግሎት ያላገኙ ሕጻናትን ላይ ያነጣጠረውን ፤ "የአማራጭ ትምህርት እና የተሻሻለ የሀገር አቀፍ የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮጀክት" ላይ የተመሠረተ ነው።
የብሔራዊ የማኅበራዊ ኢንቨስትመንት ፕሮግራም ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ አዴረሚ አዴቦዋሌ፣ የፕሮግራሙ ማስፋፊያ ሁሉንም የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ክፍሎች እና ከትምህርት ቤት ውጭ ያሉ ሕጻናትን ያጠቃልላል።
አዴቦዋሌ የገንዘብ ድጋፉን በተመለከተ፤ ኤጀንሲው የምግብ ዋጋን በገበያ ዋጋ ላይ ከመመሥረት ይልቅ በቀጥታ ከገበሬዎች፣ አቅራቢዎች እና ሰብሳቢዎች ጋር በመገናኘት ዋጋዎችን የሚወስንበት ሥርዓት እንዳዘጋጀ አስረድተዋል።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X