ሶማሊያ ረሃብን ለማጥፋት ታላቅ የግብርና መርሃ ግብር አስጀመረች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሶማሊያ ረሃብን ለማጥፋት ታላቅ የግብርና መርሃ ግብር አስጀመረች
ሶማሊያ ረሃብን ለማጥፋት ታላቅ የግብርና መርሃ ግብር አስጀመረች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.09.2025
ሰብስክራይብ

ሶማሊያ ረሃብን ለማጥፋት ታላቅ የግብርና መርሃ ግብር አስጀመረች

"እንረስ እና ሶማሊያን እናበልጽግ" የተሰኘው ፕሮግራም በሚከተሉት ዘመናዊ መፍትሄዎች ላይ ትኩረቱን አድርጓል፦

የዝናብ ውሃ ማቆር፣

ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆኑ ቴክኖሎጂዎች፣

ድርቅን የሚቋቋሙ ሰብሎች፣

የመኖ ምርት እና

ዘላቂ መስኖ ስርዓቶች።

የመርሃ ግብሩ ዋና ዋና አላማዎችም፦

ገበሬዎችን ማብቃት እና

የሀገሪቱን ሰፊ ለም መሬት መጠቀም ናቸው።

እስካሁን ዘጠኝ የእርሻ ማዕከሎች የተቋቋሙ ሲሆን ለስልጠና እና ፈጠራ አገልግሎት ለመስጠት እስከ 2029 ድረስ የማዕከሎቹን ቁጥር 100 ማድረስ ታቅዷል።

የግብርና ሚኒስቴር የግሉን ዘርፍ፣ ዳያስፖራውን እና ዓለምአቀፍ አጋሮችን በዚህ ዕቅድ ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ እየጠየቀ ነው።

በአሁኑ ጊዜ ሶማሊያ ለም መሬትና የተፈጥሮ ሃብት ቢኖራትም ባልዘመነ የግብርና አሰራርና በኢንቨስትመንት እጥረት ምክንያት አብዛኛውን የምግብ ፍጆታዋን ከውጭ ታስገባለች።

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0