የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ችሎቶችን በዲጂታል መንገድ ለመተካት እንቅስቃሴ ጀመረ
14:59 14.09.2025 (የተሻሻለ: 15:04 14.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ችሎቶችን በዲጂታል መንገድ ለመተካት እንቅስቃሴ ጀመረ
የፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ምህረት የኢትዮጵያን የፍትሕ ሥርዓት ወደ ዲጂታል ለማሸጋገር ያስችላል የተባለውን “የኤሌክትሮኒክ አቤቱታ አቀራረብ እና ሙግት” መመሪያ ማጽደቃቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
መመሪያው የሚከተሉትን ያክትታል፦
▪ የፍርድ ቤት ጉዳዮችን በዲጂታል መድረኮች እንዲያስተናግዱ ይፋዊ ፈቃድ ይሰጣል፡፡
▪ የፍርድ ሂደት ተሳታፊዎች የክስ ሰነዶችን እና ፊርማዎችን በኤሌክትሮኒክስ እንዲያቀርቡ ይጠይቃል።
▪ የምስክርነት እና የመሃላ ቃል በዲጂታል መድረኩ አማካኝነት መቅረጽ (ማቅረብ) ያስችላል፡፡
▪ ፍርድ ቤቶች ችሎቶችን ከርቀት የሚያደምጡበትን እድል ይሰጣቸዋል፡፡
▪ ምስጢራዊ ሰነዶች በአካል መቅረብ እንዳለባቸው ያስገድዳል፡፡
ወጪን ለመቀነስና ቅልጥፍናን ለማሻሻል እንደሚያግዝ የታመነበት መመሪያው ከሕዳር ወር ጀምሮ በሁሉም የፌደራል ፍርድ ቤቶች እና የፌደራል ጉዳዮችን በሚያስተናግዱ የክልል ፍርድ ቤቶች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X