በአማራ ክልል ከ51 በላይ የማዕድን ዓይነቶች መገኘታቸው ጥናቶች ማረጋገጣቸው ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበአማራ ክልል ከ51 በላይ የማዕድን ዓይነቶች መገኘታቸው ጥናቶች ማረጋገጣቸው ተገለፀ
በአማራ ክልል ከ51 በላይ የማዕድን ዓይነቶች መገኘታቸው ጥናቶች ማረጋገጣቸው ተገለፀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.09.2025
ሰብስክራይብ

በአማራ ክልል ከ51 በላይ የማዕድን ዓይነቶች መገኘታቸው ጥናቶች ማረጋገጣቸው ተገለፀ

የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ እንዳስታወቀው፣ በጥናቱ ግኝት መሠረት የግራናይት እና የማርብል ፋብሪካዎች በባሕር ዳር፣ ቡሬ፣ ደብረ ማርቆስ እና በሌሎች ከተሞች በግንባታ ላይ ይገኛሉ።

የቢሮው ኃላፊ ኃይሌ አበበ፣ የብረት ማዕድንን ሀብት በክልሉ ለማልማት በእንቅስቃሴ ላይ መሆኑን ገልፀው ይህ ማዕድን በጥራቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጥ መሆኑን ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል።

ክልሉ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት፦

🟠 100 ኪሎ ግራም ወርቅ አምርቶ ለብሔራዊ ባንክ መቅረቡ፣

🟠 ማዕድናትን ወደ ውጭ በመላክ 10 ሚሊዮን ዶላር ማስገባቱን እና

🟠 በተኪ ምርቶች 113 ሚሊዮን ዶላር ትርፍ ማግኘት መቻሉን አስታውቋል፡፡

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0