የሞተር ጀልባዎች ከቀረጥ እና ከታክስ ነጻ ሆነው እንዲገቡ መፈቀዱን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ አስታወቁ

የሞተር ጀልባዎች ከቀረጥ እና ከታክስ ነጻ ሆነው እንዲገቡ መፈቀዱን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ አስታወቁ
ሚኒስትሩ በመጪው የአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከቀረጥና ታክስ ነጻ ወደ ሀገር ማስገባት መፈቀዱን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መናገራቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
ይህ መመሪያ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ከ20 በላይ ታላላቅ ሐይቆች “የቱሪዝም መዳረሻ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ሲባል” መውጣቱ ተገልጿል፡፡
በዚህም ማንኛውም በንግድ ሥራ ላይ የተሠማራ ሰው ወደ ሀገር የሚያስገባቸው፦
የዓሣ ማጥመጃ እና የመንገደኛ የሞተር ጀልባዎች (outboard motor boats)፣
ለቱሪስት እና ለአደጋ ጊዜ የሚያገለግሉ ፈጣን ጀልባዎች (speedboats)፣
የቱሪስቶች ግልጽ ወይም ከፊል ሽፍን ጀልባዎች (Tourist excursion boats)፣
የሰዎች ማጓጓዣ ጀልባዎች (Ferries)፣
ለጥናት እና ምርምር የሚያገለግሎ ጀልባዎች (Research boats)፣
ለግል አገልግሎት የሚውሉ ጀልባዎች (Private motor boats)፣
በፀሐይ ኃይል እና በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ጀልባዎች (Eco boats)፣
ጠፍጣፋ እና ባለ ጣሪያ የሞተር ጀልባዎች (pontoon boats)
ሌሎች መሰል ለኢትዮጵያ ሐይቆች ተስማሚ የሆኑ የሞተር ጀልባዎች ቀረጥ እና ታክስ ሳይከፈልባቸው ወደ ሀገር እንዲገቡ ተፈቅዷል፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X