የእንግሊዝ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር የለንደን ተቃውሞዎች ወደ ብጥብጥ መቀየራቸውን ተከትሎ ክስ እንደሚመሠረት አስጠነቀቁ
11:12 14.09.2025 (የተሻሻለ: 11:14 14.09.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየእንግሊዝ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር የለንደን ተቃውሞዎች ወደ ብጥብጥ መቀየራቸውን ተከትሎ ክስ እንደሚመሠረት አስጠነቀቁ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የእንግሊዝ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር የለንደን ተቃውሞዎች ወደ ብጥብጥ መቀየራቸውን ተከትሎ ክስ እንደሚመሠረት አስጠነቀቁ
በለንደን በተደረገው መጠነ ሰፊ ተቃውሞ ወቅት በፖሊስ ላይ ጥቃት በመሰንዘር የተሳተፈ የትኛውም ሰው ክስ ሊመሰረትበት እንደሚችል ሚኒስትሯ ሻባና ማሕሙድ አስጠንቅቀዋል፡፡
“በፖሊስ መኮንኖች ላይ ጥቃት የሰነዘሩትን እና ጉዳት ያደረሱትን አወግዛለሁ። በወንጀል ድርጊቱ ላይ ድርሻ ያለው የተኛውም ሰው የሕግን ሙሉ ኃይል ይጋፈጣል።” ሲሉ ማሕሙድ በኤክስ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።
ቅዳሜ ዕለት፣ ሰልፈኞቹ የቅዱስ ጊዮርጊስ መስቀልን እና የ’ዩኒየን ጃክ’ ባንዲራዎችን እያውለበለቡ ወደ ዋይትሆል ከማምራታቸው በፊት በ’ረስል ስኩዌር’ ተሰባስበዋል፡፡
ቶሚ ሮቢንሰን የመራው “ዩናይት ዘ ኪንግደም” ሰልፍ ተሳታፊዎች፣ የመንግሥትን የኢሚግሬሽን ፖሊሲዎች እና የመናገር ነጻነት ገደብ አድርገው የሚመለከቷቸውን ነገሮች አውግዘዋል፡፡ ፖሊስ የእርግጫ እና የቡጥ ድብደባዎችን አስተናግዷል፡፡
ፖሊስ በኤክስ ገጹ ላይ እንዳስታወቀው “ጠርሙሶች፣ ርችቶች እና ሌሎች ተወርዋሪ ነገሮች ተወርውረዋል”፤ እስካሁን ዘጠኝ ሰዎች መታሰራቸው የተረጋገጠ ሲሆን ሌሎች ብዙዎች ሊታሰሩ ይችላሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X