የኢትዮጵያ ቡና በኪሎ 1ሺ 739 ዶላር በመሸጥ ሪከርድ ሰበረ
18:47 13.09.2025 (የተሻሻለ: 18:54 13.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ቡና በኪሎ 1ሺ 739 ዶላር በመሸጥ ሪከርድ ሰበረ
'ኢኮስ ኦፍ ዘ ፒክ' በተሰኘው የግል የጨረታ ውድድር፤ አሎ ቡና በከፍተኛ ዋጋ በመሸጥ እና በከፍታ ቦታ ለተመረተ የኢትዮጵያ ቡና ዓለም አቀፍ እውቅና አስገኝቷል።
በዝግጅቱ ላይ ከ2 ሺህ 400 እስከ 2 ሺህ 580 ሜትር ከፍታ ሥፍራ ላይ የተመረቱ 20 ልዩ የቡና ዓይነቶች ቀርበው እንደነበር የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ጨረታው ዓለም አቀፉን የቡና አፍቃሪ ማህበረሰብ ትኩረት የሳበ ሲሆን 6 ሺህ 457 ተጫራቾች ዋጋ አቅርበው አጠቃላይ 135 ሺህ 922 ዶላር የጨረታ ዋጋ ተመዝግቧል።
ውጤቱ ለኢትዮጵያ ቡና ምርት አዲስ ታሪክ እንዲያስመዘግብ ያደረገ ሲሆን ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የልዩ ቡና መሪነቷን ማጠናከር የቻለችበት ነው ተብሏል።
"ይህ የአሎ ቡና ብቻ ድል አይደለም፤ በዓለም መድረክ ለኢትዮጵያ የቡና ምርት እውቅና ማስግኘት የተቻለበት ነው" ሲሉ ጨረታውን የመሩት የአሎ ቡና ሥራ አስፈፃሚ ታምሩ ታደሰ፤ በሂደቱ ኩራት እንደተሰማቸው ገልፀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X