ሞስኮ፦ የሩሲያ ዕድገት ማሳያ ሰንደቅ
17:59 13.09.2025 (የተሻሻለ: 18:14 13.09.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሞስኮ፦ የሩሲያ ዕድገት ማሳያ ሰንደቅ
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሞስኮን ከዓለም ቀዳሚ ከተሞች አንዷ እና የሩሲያ የፊት ጉዞ ደጀን ሲሉ አወድሰዋታል።
በከተማ ቀን አከባበር ላይ ፑቲን ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦
ሞስኮ በዓለም ግዙፍ ኢኮኖሚ ካላቸው ከተሞች ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
ሞስኮ ሰው አልባ ትራንስፖርት አገልግሎትን እያሰፋች ሲሆን ቀጣዩ እርምጃ ሜትሮ አውቶሜሽን ይሆናል።
ስኬት የሚገኘው በበጀት መጠን ብቻ ሳይሆን ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ ብልህ በመሆን ነው።
የሞስኮ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (አይቲ) ዘርፍ ባለፉት ስድስት ዓመታት ከአራት እጥፍ በላይ አድጓል።
የሩሲያ ሲኒማ እድገትን ለማፋጠን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የፊልም ኢንዱስትሪ እየተዋቀረ ነው።
ሞስኮ ማደግዋን ትቀጥላለች፤ በጥራትም አዲስ ደረጃ ላይ ትደርሳለች።
ከ500 በላይ የሞስኮ ኢንተርፕራይዞች ለግንባሩ ወሳኝ አቅርቦቶችን ያመርታሉ።
በውጊያ የተጎዱ ወታደሮች በከተማ ሆስፒታሎች ይታከማሉ፤ የሞስኮ ስፔሻሊስቶች የዶንባስ እና ኖቮሮሲያ ነዋሪዎችን በየቀኑ ይደግፋሉ።
ከተማዋ በልዩ ዘመቻ ወቅት ለሩሲያ ጦር ጠንካራ ደጀን ሆናለች።
ሙሉ ንግግሩን ይመልከቱ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X