ዛምቢያ 92 በመቶ የውጭ ዕዳዋን አሸጋሸገች

ዛምቢያ 92 በመቶ የውጭ ዕዳዋን አሸጋሸገች
በዚህም በኃይል፣ በማዕድን እና በመሠረተ ልማት ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ የሚያስችል ሃብት ማግኘቷን ፕሬዝዳንት ሃካይንዴ ሂቺሌማ ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንቱ ያነሷቸው ሌሎች ነጥቦች፡-
🟠 ኢኮኖሚያዊ ዕድገት፦ እ.አ.አ ከ2021 እስከ 2024 ባለው ጊዜ ውስጥ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በዓመት በአማካይ 5.2 በመቶ ዕድገት የተመዘገበበት ሲሆን ይህም እ.አ.አ ከ2017 እስከ 2020 ከነበረው የዕድገት መጠን ጋር ሲነፃፀር የሶስት እጥፍ ብልጫ አለው።
🟠 የመገበያያ ገንዘብ አቅም እና የዋጋ ግሽበት፦ የዛምቢያ የመገበያያ ገንዘብ ክዋቻን ማረጋጋት ተችሏል። የዋጋ ግሽበት በጥር ወር ከነበረበት 23.1 በመቶ፤ በነሐሴ ወር ወደ 15 በመቶ ዝቅ ብሏል።
🟠 ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች፦ የሥራ እድል ለመፍጠር እና የሀገር ውስጥ ምርትን ለመደገፍ አዳዲስ የኢኮኖሚ ዞኖች በየአካባቢው ይቋቋማሉ።
🟠 የማዕድን ዘርፍ፦ የሞፓኒ እና የኮንኮላ ማዕድን ማውጫ ሥፍራዎች እንደገና መከፈታቸው የመዳብ ምርትን አሻሽሏል።
🟠 ኢነርጂ፦ የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎች ኪትዌ (94 ሜጋ ዋት)፣ ቺሳምባ (100 ሜጋ ዋት) እንዲሁም 300 ሜጋ ዋት የሚያመነጨው ማምባ የድንጋይ ከሰል ፋብሪካን ጨምሮ ቁልፍ ፕሮጀክቶች ዕድገት እያሳዩ ነው። የግል ዘርፍ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ማሻሻያዎች እየተካሄዱ ነው።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X