ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የእስራኤል ጥቃት ለኳታር ደህንነት እና ለቀጣናው ሀገራት ጉልህ ስጋት እንደሆነ ገለፁ
15:03 13.09.2025 (የተሻሻለ: 15:14 13.09.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የእስራኤል ጥቃት ለኳታር ደህንነት እና ለቀጣናው ሀገራት ጉልህ ስጋት እንደሆነ ገለፁ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የእስራኤል ጥቃት ለኳታር ደህንነት እና ለቀጣናው ሀገራት ጉልህ ስጋት እንደሆነ ገለፁ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኳታር መዲና ዶሃ የተፈፀመው ጥቃት ዓለም አቀፍ ሕጎችን የጣሰ ነው ሲሉ ከኳታር መሪ ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ ጋር በስልክ በተነጋገሩበት ወቅት ተናግረዋል።
በጥቃቱ ዜጎች ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሀዘን በመግለፅ፤ ለኳታር ያላቸውን አጋርነት አረጋግጠዋል ሲል ገልፍ ታይምስ ዘግቧል።
ኳታር በዓለም ዙሪያ ያሉ ግጭቶችን ለመፍታት እና ለማደራደር የምታደርገውን ጥረትም አድንቀዋል።
ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ በበኩላቸው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለኳታር ሕዝብና መንግሥት ላሳዩት አጋርነት ምስጋና አቅርበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X