የአውሮፓ ፓርላማ በእስር ላይ በሚገኘው የአየርላንድ-ቶጎ ዜጋ ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ፤ ቶጎ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደርን ለተቃውሞ ጠራች
13:14 13.09.2025 (የተሻሻለ: 20:24 13.09.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአውሮፓ ፓርላማ በእስር ላይ በሚገኘው የአየርላንድ-ቶጎ ዜጋ ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ፤ ቶጎ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደርን ለተቃውሞ ጠራች

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአውሮፓ ፓርላማ በእስር ላይ በሚገኘው የአየርላንድ-ቶጎ ዜጋ ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ፤ ቶጎ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደርን ለተቃውሞ ጠራች
ሐሙስ የጸደቀው የውሳኔ ሃሳብ ቶጎ እ.አ.አ በ2018 በተከለከሉ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ በመሳተፋቸው እና “በውስጣዊ ደኅንነት ላይ አሲረዋል” በሚል ክስ የ10 ዓመት እስር ከተላለፈባቸው 13 ግለሰቦች አንዱ የሆነው አብዱል አዚዝ ጎማ እንዲፈታ በጥብቅ አሳስቧል። ውሳኔው ጎማ "በድብቅ” እንደታሰረ እና “ማሰቃየት” ደርሶበታል በማለት ወቀሳ አቅርቧል።
የቶጎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የውሳኔ ሃሳቡን፤ "በፍርድ ሂደቱ እና በሉዓላዊነት ላይ የተቃጣ ግልፅ ጣልቃ ገብነት" እንደሆነ አደርጎ እንደሚወስደው አስታውቋል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X