የማሊ ጦር በሴጉ ክልል አሸባሪዎችን እንደደመሰሰ አስታወቀ
20:28 12.09.2025 (የተሻሻለ: 20:34 12.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የማሊ ጦር በሴጉ ክልል አሸባሪዎችን እንደደመሰሰ አስታወቀ
በአካባቢው የታጠቁ ሰዎች መኖራቸውን የደህነነት መረጃ ካመላከተ በኋላ ዘመቻው መጀመሩን ያሳወቀው መግለጫ፤ ቡድኑን ለማስወገድ የጦር ኃይሎች ጓድ ወደ ሥፍራው በማቅናት እርምጃ መውሰዱን ገልጿል።
በተካሄደው ኦፕሬሽን አስር የሚጠጉ ታጣቂዎች መያዛቸውን ይፋ ያደረገው ሠራዊቱ፤ የጦር መሳሪያዎችና ሞተር ሳይክሎችን ጨምሮ ከፍተኛ መጠን ያለው ንብረት በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቋል።
ተጨማሪ የፍለጋ እና አካባቢውን የማጥራት ሥራዎች አሁንም በመካሄድ ላይ መሆናቸውን በመግለጫው ተጠቁሟል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X