- Sputnik አፍሪካ, 1920
Sovereignty Sources
ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣

የታላቁ የህዳሴ ግድብ፡ የኢትዮጵያ የኃይል ሚዛን ገፀ በረከት

የታላቁ የህዳሴ ግድብ፡ የኢትዮጵያ የኃይል ሚዛን ገፀ በረከት
ሰብስክራይብ
'የናይል ተፋሰስ ውስጥ ያለው አመለካከት ሁለት ነው። ውኃ አመንጫ ሀገራት የውኃ መብት አለን፣ ውኃው የሁላችንም የጋራ ሐብት ነው። በትብብር ብናለማው ለሁላችንም ይጠቅማል የሚል ሀሳብ ነው ያላቸው - ሁለት የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ውኃው ሙሉ ለሙሉ የኛ ነው የሚገባው የሚሉ ናቸው - ሲሉ ከህዳሴ ግድብ ተደራዳሪዎች አንዱ ዶ/ር ያዕቆብ አርሳኖ አቲቶ ተናግረዋል።''
የአፍሪካ ጉዳዮች ተመራማሪው ዶ/ር ጋሻው አይፈራም በበኩላቸው፡-
'የናይል ወንዝ ለኢትዮጵያ ጂኦ ፖለቲካዊ ጠቀሜታ አለው። ኢትዮጵያ ቀጠናው ላይ የምትጫወተውን ሚና ከፍ ሊያደርግ ይችላል። የምጣኔ ሐብታዊ ጠቀሜታም አለው - ብለዋል።'
የታላቁ የህዳሴ ግድብ በሰፊው የህዘብ ተሳትፎ ተገንብቶ በይፋ መመረቁ በናይል ተፋሰስ ሀገራት እና በአጠቃላይ የአፍሪካ አህጉር የጂዮፖለቲካ ከባቢ ላይ ስለሚፈጥረው የኃይል ሚዛን ለውጥ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ለመወያየት የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ተራዳሪ ከነበሩት መካከል ዶ/ር ያቆብ አርሳኖ አቲቶ እና የአፍሪካ ጉዳዮች ተመራማሪውን ዶ/ር ጋሻው አይፈራምን ጋብዟቸው በጥልቀት አወያይቷቸዋል።
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsAfripodsDeezerPocket CastsPodcast AddictSpotify
አዳዲስ ዜናዎች
0