የታንዛኒያ የጸረ-ሙስና ጥረቶች ልማትና የሕዝብ አግልግሎትን እየደገፉ ነው - የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት
18:28 12.09.2025 (የተሻሻለ: 18:34 12.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የታንዛኒያ የጸረ-ሙስና ጥረቶች ልማትና የሕዝብ አግልግሎትን እየደገፉ ነው - የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት
ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን በንዝጋ ከተማ ለደጋፊዎቻቸው ባደረጉት ንግግር መንግሥታቸው ለጸረ-ሙስና የሰጠው ትኩረት በጀቶች ቁልፍ ለሆኑ የማህበረሰብ ፕሮጀክቶች፤ ማለትም፦
🟠 ለመንገዶች፣
🟠 ለውሃ መሠረተ ልማት፣
🟠 ለሆስፒታሎች፣
🟠 ለአርሶ አደሮች ድጋፍ እንዲውሉ አስችሏል ብለዋል፡፡
የመንግሥት ሠራተኛው የቅርብ ክትትል ኃላፊነት የተሞላበት የሀብት አጠቃቀምን እንዳገዘም አንስተዋል፡፡
ሳሚያ ሀሰን ከሩዋንዳ በመቀጠል በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ዝቀተኛ የሙስና ምጣኔ ያለባት ሀገር በሚል የተሰጠውን ደረጃ በመጥቀስ የታንዛኒያ ለውጥ ዓለም አቀፍ እውቅና ተችሮታል ሲሉ አስረግጠዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

