ከኢትዮጵያ ጋር ያለን ግንኙነት ይበልጥ እየተጠናከረ ይሄዳል ብለን እንጠብቃለን - የቤላሩስ ፕሬዝዳንት

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱከኢትዮጵያ ጋር ያለን ግንኙነት ይበልጥ እየተጠናከረ ይሄዳል ብለን እንጠብቃለን - የቤላሩስ ፕሬዝዳንት
ከኢትዮጵያ ጋር ያለን ግንኙነት ይበልጥ እየተጠናከረ ይሄዳል ብለን እንጠብቃለን - የቤላሩስ ፕሬዝዳንት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 12.09.2025
ሰብስክራይብ

ከኢትዮጵያ ጋር ያለን ግንኙነት ይበልጥ እየተጠናከረ ይሄዳል ብለን እንጠብቃለን - የቤላሩስ ፕሬዝዳንት

ፕሬዝዳንት ሉካሼንኮ በቤላሩስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ገነት ተሾመን ሹመት በተቀበሉበት ወቅት የተናገሩት ነው፡፡

"በካዛን ከብሪክስ የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ግንኙነታችንን ለማሳደግ ስምምነት ላይ የተደረሰባቸው ጉዳዮች በተቻለ ፍጥነት እንደሚተገበሩ እጠበቃለሁ፡፡... የጋራ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅተን ከግብርና ማሽነሪ፣ በቤላሩስ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን ተቀበሎ እስከ ማሠልጠን ድረስ በሁሉም ዘርፍ መሥራት ይኖርብናል" ሲሉም አሌክሳንደር ሉካሼንኮ አክለዋል፡፡

የቤላሩስ መሪ ኢትዮጵያን በምስራቅ አፍሪካ የቤላሩስ የረጅም ጊዜ እና ታማኝ አጋር ሲሉ ገልፀዋታል።

"ለኢትዮጵያ ገለልተኛ የውጭ ጉዳይ መርህ ትልቅ አክብሮት አለን። በቁልፍ ዓለም አቀፍ አጀንዳዎች ላይ ያላችሁን በመርህ ላይ የተመሠረተ አቋም እንገነዘባለን፤ እንጋራችኋለንም" ብለዋል፡፡

አምባሳደር ገነት ተሾመ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የግብርና ዘርፉን ለማዘመን ከቤላሩስ ጋር የጀመረችውን ወዳጅነት አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0