“ሞቃዲሾ በአስርት ዓመታት ውስጥ ከመቼውም ግዜ በላይ አስተማማኝ ደህንነት ላይ ትገኛለች” ሲሉ የሶማሊያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ
15:03 12.09.2025 (የተሻሻለ: 15:04 12.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
“ሞቃዲሾ በአስርት ዓመታት ውስጥ ከመቼውም ግዜ በላይ አስተማማኝ ደህንነት ላይ ትገኛለች” ሲሉ የሶማሊያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ
በሀገሪቱ ዋና ከተማ የፀጥታ ችግር በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሳላህ ጃማ፤ የሶማሊያ የፀጥታ ኃይሎች፣ ዓለም አቀፍ አጋሮች እና ህብረተሰቡ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ላሳየው ፅናትና ጥንካሬ ምሥጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
"አንድ ሰው፤ አንድ ድምጽ" መርህ ላይ መሠረት ያደረገው ቀጥተኛ ምርጫ፤ የፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አካል ሆኖ በሂደት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ ጠንካራ ተቋማትን መገንባት ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ እና የሶማሊያን ገፅታ ለማሻሻል ቁልፍ ተግባራት ተደርገው ይወሰዳሉ ሲሉም ገልፀዋል።
"የ2025ቷ ሶማሊያ ከምጣኔ ሀብት እስከ ደህንነት፣ ከዓለም አቀፍ ግንኙነት እስከ ማህበራዊ ትስስር ድረስ በሁሉም ዘርፎች እያደገች ያለች ሀገር ነች" ሲሉም ጃማ ተናግረዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X