የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ም/ፐሬዝዳንት ሪክ ማቻር በሀገር ክህደት፣ በነፍስ ግድያ እና ሰብዓዊነት ላይ በተፈፀሙ ወንጀሎች ክስ ቀረበባቸው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ም/ፐሬዝዳንት ሪክ ማቻር በሀገር ክህደት፣ በነፍስ ግድያ እና ሰብዓዊነት ላይ በተፈፀሙ ወንጀሎች ክስ ቀረበባቸው
የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ም/ፐሬዝዳንት ሪክ ማቻር በሀገር ክህደት፣ በነፍስ ግድያ እና ሰብዓዊነት ላይ በተፈፀሙ ወንጀሎች ክስ ቀረበባቸው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 12.09.2025
ሰብስክራይብ

የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ም/ፐሬዝዳንት ሪክ ማቻር በሀገር ክህደት፣ በነፍስ ግድያ እና ሰብዓዊነት ላይ በተፈፀሙ ወንጀሎች ክስ ቀረበባቸው

ሪክ ማቻር በመጋቢት ወር የፌደራል ኃይሎች ላይ በተፈፀመው ጥቃት በነበራቸው ተሳተፎ ክሱ እንደተመሠረተባቸው የደቡብ ሱዳን ፍትሕ ሚኒስትር ጆሴፍ ጋናግ ሐሙስ ዕለት አስታውቀዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማቻርን ከሥልጣን እንዳነሱ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል። በተጨማሪም ከማቻር ጋር ክስ የቀረበባቸው የነዳጅ ሚኒስትሩ ፑኦት ካንግ ቾልን ከሃላፊነታቸው ማሰናበታቸው ተገልጿል፡፡

ማቻር የነጭ ጦር ታጣቂዎች በናስር ከተማ ከሰነዘሩት ጥቃት ጋር ተያይዞ ከመጋቢት ወር ጀምሮ በቁም እስር ላይ ይገኛሉ።

ነጭ ጦር ማቻርን ጨምሮ በሱዳን ሕዝቦች ነፃ አውጪ ንቅናቄ/ሠራዊት መሪዎች ትዕዛዝ ይንቀሳቀስ እንደነበር ጆሴፍ ጋናግ ገልፀዋል፡፡ ከማቻር በተጨማሪ 20 ሰዎች ክስ እንደተመሠረተባቸውና 13 ሰዎች ገና በቁጥጥር ስር እንዳልዋሉ ጠቁመዋል።

በእንግሊዝኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0