በአፍሪካ ግዙፉን አውሮፕላን ማረፊያ እ.አ.አ በ2030 አጠናቆ አገልግሎት ለማስጀምር ግብ ተይዟል - የኢትዮጵያ አየር መንገድ
11:54 12.09.2025 (የተሻሻለ: 12:04 12.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በአፍሪካ ግዙፉን አውሮፕላን ማረፊያ እ.አ.አ በ2030 አጠናቆ አገልግሎት ለማስጀምር ግብ ተይዟል - የኢትዮጵያ አየር መንገድ
ዋና ሥራ አስፈፃሚው መስፍን ጣሰው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን በ2018 በጀት ዓመት ለማስጀመር ዝግጅቱ እንደተገባደደ እና በሥፍራው ይኖሩ የነበሩ አርሶ አደሮችን ወደ አዲስ ቦታ ለማዘዋወር እየተገነቡ ያሉ ቤቶች እየተጠናቀቁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
የሚገነባው አዲስ አየር ማረፊያ፦
◻ እጅግ ዘመናዊ ተርሚናል እንደሚኖረው፣
◻ ከዓለም ታላላቅ አውሮፕላን ማረፊያዎች ተርታ እንደሚሰለፍ፣
◻ አየር መንገዱን ከዓለም ስመ ገናናዎች አንዱ እንደሚያደርገው ተናግረዋል፡፡
ዋና ሥራ አስፈፃሚው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከራዕይ 2035 ወደ 2040 እየተሸጋገረ እንደሚገኝም አስታውቀዋል፡፡
የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ሥራ ሲገባ፤ የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ማሻሻያ ተደርጎለት ለሀገር ውስጥ በረራዎች እንደሚውል ዋና ሥራ አስፈፃሚውን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X