ሞስኮ ከሶማሊያ ጋር የሚኖራትን ሁለንተናዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት በሂደት ለማሳደግ አቅዳለች - የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
11:10 12.09.2025 (የተሻሻለ: 11:34 12.09.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሞስኮ ከሶማሊያ ጋር የሚኖራትን ሁለንተናዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት በሂደት ለማሳደግ አቅዳለች - የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሞስኮ ከሶማሊያ ጋር የሚኖራትን ሁለንተናዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት በሂደት ለማሳደግ አቅዳለች - የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
የሁለትዮሽ ግንኙነቱ በጋራ መከባበር ላይ የተመሠረተ መሆኑን ያነሱት ማርያ ዛካሮቫ፤ ሁለቱ ሀገራት በበርካታ ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ አመለካከት እንዳላቸው ገልፀዋል።
“በቀጣይ በሚኖረን ግንኙነት ላይ እርግጠኞች ነን፤ ለሶማሊያ ሕዝብ ሰላም እና ብልፅግና እንመኛለን” ሲሉም ተናግረዋል።
የሩሲያ እና ሶማሊያ ዲፕሎምሲያዊ ግንኙነት 65ኛ ዓመት መስከረም 1 ተከብሯል፡፡ ዛካሮቫ አክለውም ሶቪዬት ህብረት ለሶማሊያ ነፃነት እውቅና በመስጠትና በመንግሥተ ምስረታ ላይ ቀዳሚ አስተዋጽኦ አድርጋለች ብለዋል፡፡
ሞስኮ የቀድሞ ፕሬዝዳንቶችን ጨምሮ ከ20 ሺህ ለሚበልጡ ሶማሊያውያን መሳሪያ፣ መሠረተ ልማቶች በማቅረብ እና ሥልጠና በመስጠት የሀገራቱን ትብብር ስትደግፍ መቆየቷን አስታውሰዋል፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X