ሮስቴክ አዲስ ፀረ-ድሮን ቴክኖሎጂ ይፋ አደረገ
19:18 11.09.2025 (የተሻሻለ: 19:24 11.09.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሮስቴክ አዲስ ፀረ-ድሮን ቴክኖሎጂ ይፋ አደረገ
አዲሱ "ድቪና-100ኤም" ፀረ-ድሮን ስርዓት የጠላት ድሮኖች ጥቃት የመፈፀም አቅምን ያመነመነ ነው ተብሏል።
ቴክኖሎጂው በቅዝቃዜም ይሁን በከፍተኛ ሙቀት ወቅት የጠላት ድሮኖችን አቅጣጫ ጠቋሚ ስርዓት በመቁረጥ ከጥቅም ውጪ እንደሚያደርግ የሩሲያው ሮስቴክ አስታውቋል።
ምን ተግባራት ያከናውናል፦
▪ ሁሉንም የድሮን ማገናኛዎች ያግዳል — በየተኛው የአየር ሁኔታ (ከ-40°ሴ እስከ +50°ሴ) የቁጥጥር፣ የተንቀሳቃሽ ምሥል እና የጂፒኤስ ምልክቶችን ያቋርጣል።
▪ ስማርት ድሮኖችን ይጠልፋል — ራሳቸውን ለመደበቅ መለያ ቁጥራቸውን የሚቀያይሩትንም ጭምር ያስቆማል።
▪ ኢላማውን በመቆለፍ፤ በትክክል ይጠልፋል — መጀመሪያ በማዳመጥ የድሮኑን ትክክለኛ ምልክት ብቻ ይጠልፋል።
▪ የትኛውንም የድሮን ዓይነት ያስቆማል — ለብቻቸው የሚበሩ፣ በጋራ የሚበሩ አልያም የመጠባበቂያ ቁጥጥር የሚደረግባቸው የተሻሻሉ ሞዴሎችን ጭምር ያስቆማል።
▪ ሰፊ ቦታዎችን ይጠብቃል — በመቶ ሜትሮች ስፋት ያለው ከባቢን መከላከል መቻሉ ለአውሮፕላን ማረፊያዎች፣ ጣቢያዎች እና ፋብሪካዎች ምቹ ያደርገዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X