ጋቦን ባንኮች እና የፋይናንስ ተቋማት በብቸኝነት በዜጎቿ እንዲመሩ ውሳኔ ልታሳልፍ ነው
18:53 11.09.2025 (የተሻሻለ: 18:54 11.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ጋቦን ባንኮች እና የፋይናንስ ተቋማት በብቸኝነት በዜጎቿ እንዲመሩ ውሳኔ ልታሳልፍ ነው
ውሳኔው ተግባራዊ ሲሆን የውጭ ሀገር ዜጎች የፋይናንስ ተቋማትን እንዲመሩ የሚፈቀድላቸው በብሔራዊ ኢኮኖሚ እና ፋይናንስ ኮሚቴ ልዩ ፈቃድ ሲያገኙ ብቻ ነው ሲል የሚኒስትሮች ምክር ቤት በመግለጫው አስታውቋል።
ይህ እርምጃ በአመራር ቦታ ላይ ያለውን የውጭ ዜጎች የበላይነት በመግታት ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነትን ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል።
እንደ ሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘገባ መንግሥት፦
🟠 በሀገር አቀፍ ደረጃ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ጋር የተጣጣመ አስተዳደርን ለማበረታታት፣
🟠 በባንክ ዘርፍ ላይ ያለውን እምነት ለመመለስ፣
🟠 የብድር አቅርቦት ተግዳሮቶችን ለመፍታት ውጥን አስቀምጧል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X