ናይጄሪያ እ.አ.አ በ2035 የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ ከ10 በመቶ ወደ 25 በመቶ ለማሳደግ አቅዳለች
18:31 11.09.2025 (የተሻሻለ: 18:34 11.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ናይጄሪያ እ.አ.አ በ2035 የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ ከ10 በመቶ ወደ 25 በመቶ ለማሳደግ አቅዳለች
ይህ ውጥን የናይጄሪያን ኢኮኖሚ ተፈጥሮአዊ ሀብት ላይ ከተመሠረተ ወደ ምርታማ፣ ተወዳዳሪ እና ፈጠራን ያማከለ ለማድረግ ያለመ የመንግሥት አዲስ ስትራቴጂክ ማዕቀፍ አካል ነው ሲሉ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሴኔተር ጆን ኦዋን ተናግረዋል።
"ናይጄሪያ ዝግጁ ነች። አፍሪካ አዲሲቷ ቀጣና ናት፤ እኛም ዓለም አቀፍ ቅድመ ሁኔታዎችን ለማሟላት ማሻሻያ እያደረግን ነው።...በታሪካችን ከአሁኑ የተሻለ ጊዜ የለም። ናይጄሪያ ክፍት እና ለንግድ ዝግጁ ነች" ሲሉ ኦዋን በጣሊያን ሚላን እየተካሄደ በሚገኘው የጋዝቴክ ኤግዚቢሽን እና ኮንፈረንስ ላይ መናገራቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ሚኒስትሩ እቅዱን የፕሬዝዳንት ቲኑቡ አስተዳደር ጉልህ ስኬት ነው ሲሉ ገልፀውታል። የነዳጅ ድጎማ መነሳት፣ የምንዛሪ ዋጋን ማጣጣምና ኢኮኖሚውን ማረጋጋት ጨምሮ የፕሬዝዳንቱን የለውጥ እርምጃዎች በአድናቆት አንስተዋል።
ናይጄሪያ ባላት ሰፊ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ላይ ትኩረት ሰጥታ እየሠራች ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ልማትን ለማፋጠን እና ሀገሪቱን በዓለም አቀፍ ገበያ ዘላቂ አቅራቢ ለማድረግ አቅዳ እየሠራች መሆኑን ጠቁመዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X