ሩሲያ የፍልስጤምን ጉዳይ ለመፍታትና የፍልስጤማውያንን መብት ለማስጠበቅ የምታደርገውን ጥረት ኳታር ታደንቃለች - የኳታር ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
15:40 11.09.2025 (የተሻሻለ: 15:44 11.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ የፍልስጤምን ጉዳይ ለመፍታትና የፍልስጤማውያንን መብት ለማስጠበቅ የምታደርገውን ጥረት ኳታር ታደንቃለች - የኳታር ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
የኳታር ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱልጣን አብዱላዚዝ አል ሙራይኪ ይህንን ያሉት፤ በሶቺ በተካሄደው የሩሲያ-ባሕረ ሰላጤ የትብብር ምክር ቤት የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ በሰጡት መግለጫ ነው።
የሚኒስትሩ ተጨማሪ ቁልፍ መግለጫዎች፦
🟠 ኳታር ለመካከለኛው ምስራቅ አለመረጋጋት እስራኤልን ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ አድርጋለች።
🟠 ኳታር በጋዛ ሰርጥ የተኩስ አቁም ለማሳካት ጥረቷን ትቀጥላለች።
🟠 ዶሃ በኔታኒያሁ በሚመራው የእስራኤል አገዛዝ መንግሥታዊ ሽብርተኝነት ተፈፅሞባታል። ሀገሪቱ በእስራኤል ጥቃት ዙሪያ ሁሉንም ሕጋዊ እርምጃዎች መውሰድ ጀምራለች።
🟠 የባሕረ ሰላጤዋ ሀገር የሕዝቦችን የራስን እድል በራስ የመወሰንና የመከበር መብት ለማስጠበቅ፤ ከስትራቴጂክ አጋሮቿ ጋር በመተባበር ፍትሕን ለማስፈን እና ዓለም አቀፍ ሕጋዊነትን ለማፅናት ትሠራለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X