የዚምባብዌ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ከአሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ መቋረጥ በኋላ ወሳኙን የወባ መከላከያ ፕሮግራም አስቀጠለ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየዚምባብዌ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ከአሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ መቋረጥ በኋላ ወሳኙን የወባ መከላከያ ፕሮግራም አስቀጠለ
የዚምባብዌ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ከአሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ መቋረጥ በኋላ ወሳኙን የወባ መከላከያ ፕሮግራም አስቀጠለ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 11.09.2025
ሰብስክራይብ

የዚምባብዌ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ከአሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ መቋረጥ በኋላ ወሳኙን የወባ መከላከያ ፕሮግራም አስቀጠለ

ዩኒቨርስቲው ወሳኝ የወባ ምርምር እና ቁጥጥር መርሃ-ግብሩን፤ የአሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ ሥራውን እንዲያቆም ካስገደደው ወራት በኋላ አስጀምሯል።

የዚምባብዌ የነፍሳት ጥናት ድጋፍ በመባል የሚታወቀው ይህ የወባ ፕሮግራም (ዜንቶ)፤ የሀገሪቱ ግንባር ቀደም የወባ ክትትል ማዕከል ሲሆን አሁን ከተባበሩት የሜቶዲስት ቤተ-ክርስቲያን የግሎባል ሚንስትሪ ቦርድ የአደጋ ጊዜ የገንዘብ ድጋፍ ተደርጎለታል።

"ይህ በዚምባብዌ ለሚሊዮኖች ተስፋን የሚመልስ ነው። 70 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ በገዳይ የፋልሲፓረም ወባ ስጋት ውስጥ ነው ያለው" ሲሉ የፕሮግራሙ ዳይሬክተር ሱንጋኖ መሃራኩርዋ ተናግረዋል።



ዜንቶ የፀረ-ተባይ መቋቋምን በመከታተል፣ የመከላከያ ዘመቻዎችን በመምራት እና የመጪው ግዜ ሳይንቲስቶችን በማሠልጠን ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታል።

አዲሱ የአራት ዓመት ፕሮግራም ዜንቶ ብሔራዊ የወባ መከላከል ግቦችን መደገፉን እንዲቀጥል ያስችለዋል ተብሎ ይጠበቃል።

በእንግሊዝኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0