"የባሕረ ሰላጤ ምክር ቤት አባል ሀገር ላይ የሚደረግ ጥቃት በጠቅላላ ድርጅቱ ላይ እንደተቃጣ ይቆጠራል" - የኩዌት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
14:37 11.09.2025 (የተሻሻለ: 14:44 11.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
"የባሕረ ሰላጤ ምክር ቤት አባል ሀገር ላይ የሚደረግ ጥቃት በጠቅላላ ድርጅቱ ላይ እንደተቃጣ ይቆጠራል" - የኩዌት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
እስራኤል ኳታር ላይ የሰነዘረችው ጥቃት አደገኛ መካካር እና ዶሃ በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም ለማስፈን የምታደርገውን ጥረት የሚያደናቅፍ መሆኑን አብዱላህ አሊ አል ያህያ ተናግረዋል።
በሶቺ በተካሄደው የሩሲያ-ባሕረ ሰላጤ ትብብር ምክር ቤት የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ የኩዌት ውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ቁልፍ መግለጫዎች፡-
▪የእስራኤል ወረራ ሳይቆም እና ነጻ የሆነች ሀገረ ፍልስጤም እስካልተመሠረተች ድረስ ዘላቂ መረጋጋት ሊኖር አይችልም።
▪ኩዌት እስራኤል በጋዛ ሰርጥ የምትከተለውን የረሃብ እና ዜጎችን የማፈናቀል ፖሊሲ በድጋሚ ታወግዛለች።
▪የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ጋዛ እንዳይገባ የተጣለውን ገደብ ማንሳት አስፈላጊ እንደሆነ አጽንኦት ትሰጣለች።
▪መጪው የሩሲያ እና የአረብ ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ በትብብር እና ግንኙነት ዙሪያ ለሁለቱ ወገኖች ፍሬያማ ውጤት እንደሚያስገኝ ኩዌት ተስፋ ታደርጋለች።
ℹ በታሪክ የመጀመሪያው የሩሲያና የአረብ ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ እ.ኤ.አ ጥቅምት 15 በሞስኮ ይካሄዳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X