የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ተነሳሽነቶች አወደሰ
14:23 11.09.2025 (የተሻሻለ: 14:24 11.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ተነሳሽነቶች አወደሰ
የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ትግበራ ረዳት ዋና ፀኃፊ ሴልዊን ሃርት፤ ኢትዮጵያ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እና የኃይል አቅርቦት እንቅስቃሴ ለዓለም ማሳያ እንደሆነች ተናግረዋል።
የኢትዮጵያን የአየር ንብረት ለውጥ ፖሊሲዎች ያደነቁት ሴልዊን ሃርት፤ የአህጉሪቱ ሰፊ የንፁህ ኢነርጂ አቅም በኢንቨስትመንት እና በፖሊሲ ድጋፍ እጦት እንደተስተጓጎለ አጽንኦት ሰጥተዋል።
የአፍሪካን ብልፅግና እና የኃይል ነፃነት ለማረጋገጥ ሁሉም ሀገራት አዲስ ብሔራዊ የአየር ንብረት ትግበራ እቅዶችን ወደ ሥራ እንዲያስገቡ ጠይቀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X