የቱኒዚያ እና የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለጋዛ የተኩስ አቁም፣ ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ እና የፍልስጤም ሀገርነት ጥሪ አቀረቡ
13:41 11.09.2025 (የተሻሻለ: 13:44 11.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የቱኒዚያ እና የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለጋዛ የተኩስ አቁም፣ ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ እና የፍልስጤም ሀገርነት ጥሪ አቀረቡ
ሞሀመድ አሊ እና የኢራኑ አቻቸው አባስ አርጋቺ በመካከለኛው ምስራቅ ሁኔታዎች እና ሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን የቱኒዚያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሁለቱ ሚኒስትሮች ስምምነት የደረሱባቸው ጉዳዮች፦
▪በፍልስጤማውያን ላይ የሚፈፀሙ የጭካኔ ጥቃቶች እንዲቆሙ፣
▪በጋዛ እና በሁሉም የፍልስጤም ግዛቶች ላይ ስቃይ እንዲያበቃ፣
▪የሰብዓዊ እርዳታ ያለምንሞ ቅድመ ሁኔታና ገደብ ተደራሽ እንዲሆን፣
▪የፍልስጤማውያን መሉ የታሪክ መብት እንዲደገፍ፣
▪በራሳቸው መሬት ላይ ነፃ ሀገር እንዲገነቡ።
ውይይቱ ሳይንስ፣ ባሕል፣ ቱሪዝምና ጤናን ጨምሮ በጋራ ሊሠሩባቸው በሚችሉ ጉዳዮች ላይም ያተኮረ እንደነበር ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

