የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ የ "አዲስ አበባ የስምምነት ሰነድ" ን በማፅደቅ ተጠናቀቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ የ "አዲስ አበባ የስምምነት ሰነድ" ን በማፅደቅ ተጠናቀቀ
የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ የ አዲስ አበባ የስምምነት ሰነድ ን በማፅደቅ ተጠናቀቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 11.09.2025
ሰብስክራይብ

የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ የ "አዲስ አበባ የስምምነት ሰነድ" ን በማፅደቅ ተጠናቀቀ

ሰነዱ አህጉሪቱ የውስጥ መፍትሄዎችን ለማራመድ እና ፍትሐዊ የአየር ንብረት ፋይናንስን ለማረጋገጥ ያላትን የጋራ ቁርጠኝነት ያመለከተ ነው ተብሏል።

የአፍሪካ መሪዎች ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት ተፈጥሮን መሠረት ያደረጉ መፍትሄዎች ላይ አፅንዖት ሰጥተው እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል።

በኢትዮጵያ ተግባራዊ የተደረገው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ተመሳሳይ ሥራዎችን ለመሥራት የሚያነሳሳ አህጉራዊ ማሳያ በሚል እውቅና ተሰጥቶታል።

የጋራ የስምምነት ሰነዱ፦

የአፍሪካ ኅብረት ታላቁ አረንጓዴ ግንብ ኢኒሼቲቭ፣

የአፍሪካ መሬቶችን መልሶ ማቋቋም፣

የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ፣

ቁልፍ አፍሪካዊ ውጥኖችን በማስፋት የተጠናከረ ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንዲኖር ይጠይቃል።

🟢 የአፍሪካ የአየር ንብረት ፈጠራ ኮምፓክት ይፋ የተደረገም ሲሆን መሪዎች የአህጉሪቱን ድምጽ በማሰማት ለአየር ንብረት ቀውስ መፍትሄዎች ዓለም አቀፋዊ ምላሸ እንዲሰጥ በማድረግ ቃል ኪዳናቸውን ወደ ተግባር ለመቀየር አንድነታቸውን አረጋግጠዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0